SPORTS

በኦታዋ የ 10 ኪ.ሜ የሩጫ ውድድር ኢትዮጵያኖች በሁለቱም ጾታዎች አሸነፉ
 May 28, 2017
 
በኦታዋ በተደረገው የ 10 ኪ ሜ የጎዳና ውድድር ኢትዮጵያዊያን ሯጮች ነጻነት ጉደታ እና ልኡል ገ/ስላሴ በሁለቱም ጾታዎች አሸናፊ ሆኑ። ሶስት ኪ ሜ ብቻ ከተፎካካሪዎቿ ጋር አብራ የሮጠችው ነጻነት ጉደታ ከሰባተኛ ኪ ሜ በኋላ ለብቻዋ በመገንጠል ውድድሩን በተደላደለ መልኩ 31.35 በመሮጥ አሸናፊ ሆናለች። ሁለቱ ኬኒያዎች ፓስካሊ ቺፕኮሪር እና ሞኒካ ኒጂጂ ነጻነትን ተከትለው ውድድሩን ለማጠናቀቅ 32.08 እና 32.46 ፈጅቶባቸዋል።ነ

ጻነት አሸናፊ ስትሆን ከተከታይ ኬኒያዊ ተፎካካሪዎቿ ከ 33 ሰከንድ በላይ ቀድማ በመግባት ነበር። ሶስት ደቂቃ ከ 10 ሰከንድ ከወንዶች ቀደም ብሎ የጀመረው የሴቶቹ ውድድር ሴቶቹ ከወንዶቹ ጋር የመፎካከር እድል የተፈጠረላቸው ሲሆን የወንዶቹ አሸናፊ ልኡል ገ/ስላሴ ነጻነት ላይ ለመድረስ ሙከራ ቢያደርግም ውድድሩን ለማጠናቀቅ የቻለው ከሴቶቹ አሸናፊ በስምንት ሰከንድ ዝቅ ብሎ 28.43 በማስመዝገብ ነበር። “ውድድሩን በማሸነፌ በጣም ተደስቻለው።ከመጀመሪያው ጀምሮ በራሴ ስለተማመንኩ ከወንዶቼ ቀድሜ መጨረስ እንደምችል ተሰምቶኝ ነበር።” ስትል ለቀረበላት ጥያቄ ምላሿን ጀምራለች። 

በውድድሩ መሀል ደጋግማ ሰአቷን የተመለከተችበት እንዲሁን ከኋላዋ የሚከተላት መኖሩን እየዞረች ለመመልከት የሞከረችበትን ሂደት ታስታውሳለች”ያንን ማድረጌ በፍጥነት እንድሮጥ ረድቶኛል ስለዚህ ከወንዶች ጋር እንድፎካከር አድርጎኛል።ከኋላዮ ማን እየተከተለኝ እንዳለ ለመመልከት ሞክሪያለሁኝ፣ አንድ ጊዜ ከሴቶቹ ሯጮች ቀድሜ ከወጣው በኋላ ትኩረቴን ያደረኩት ለወንዶቹ ሯጮች ነበር።” በማለት ምላሿን አጠናቃለች። ውድድሩን በአንደኝነት በማጠናቀቋ የ 8000 ሺ ዶላር ስትሸለም ከወንዶች ቀድማ በመግባቷ ደግሞ ተጨማሪ ጉርሻ ታገኛለች። 

(ምንጭ : ኢትዮ አዲስ ስፖርት )
__________________________________

ጥሩነሽ ዲባባ የግሬት ማንችስተር ማራቶን አሸናፊ ሆነች

May 28, 2017







(ምንጭ : ኢትዮ አዲስ ስፖርት ) 

__________________________

No comments: