Sunday, 14 July 2019

አዴፓ ውስጡ ሲፋቅ የድሮ ኢሰፓ መሆኑን ኣሁን ጋሃድ ሆነዋል


ፍስሃ መረሳ 

የኣገራችን ታሪክ መለስ ብለን ስናስታውስ በተለያየ ጊዜ ስልጣን ይዘው ያስተዳደሩ የነበሩ የኢትዮጵያ ገዥ መደቦች የራሳቸውን ጥቅም ለማስጠበቅ ብለው በህዝቡ ላይ ስፍር ቁጥር የሌለው ግፍና በደል እንዳደረሱ የትናንቱ የማይረሳና በህዝቦች ትግል የተገረሰሰው የደርግ ስርአት ብቻ ማስተወስ በቂ ይሆናል ፡፡ በየጊዜው የህዝብ ስልጣን በሃይል የተቆጣጠሩት እነዚህ ፀረ ህዝብ ሃይሎች የነሱ አላማ ሁሌም የብዙሃንን መብትና ጥቅም በመጨፍለቅ ጥቂቶች በህዝብ ሃፍት የሚከብሩበትና የሚፈነጩበት ፖለቲካዊ ስርኣት መፍጠርና እነሱ እንዳሻቸው የሚያደርጓት ኣገር እንድትኖር ማድርግ ነው የወትሩ ህልማቸው ፡፡ እነሱ ይከተሉት በነበሩት ኣድላዊና ኢ-ፍትሃዊ ፖሊሲም ኣገራችን ከ28 ዓመት በፊት የነበራት ታሪክ እንደሚታወቀው ከኣለም የድሃ ድሃ ኣገር ተብላ የምትታወቅ ኣገር እንደነበረች ኣለም ያወቀው ለማንም  የማይደበቅ የመጥፎ ገፅታችን ማሳያ እንደሆነ ሁላችን የማንክደው የኣደባባይ ሃቅ ነው ፡፡ 

የኢትዮጵያ ህዝቦች በከፈሉት ከባድ መስዋእትነት የደርግን ስርኣት ገርስሰው ይህ አሳፋሪ ታሪካችን የሚቀይር ኣዲስ ዘርፈ ብዙ የአገር ግንባታ ጉዞ ኣለምን ባሰገረመ ፍጥነት ጀምረን ባሳለፍነው ሁለት አስርት አመታት ቀላል የማይባል ይቅር ወዳጅ ጠላትም የማይክደው ተጨባጭ ለውጥ ማመጣት ከጀመርና በኃላ በኢህአዴግ አማራር በተፈጠረ የኣመራር ክፍተት ስርአቱን ሊቀለብስ የሚችል ፅንፈኛ ቡዱን ስልጣኑን የሚቆጣጠርበት መጥፎ አጋጣሚ በመፈጠሩ እነሆ ኣገራችን ከባለፈው ኣመት ጀምሮ ወደ መውጫ የሌለው ቀውስና ትርምስ ገብታ በኣፍሪካ የሰላም የመቻቸልና የመከባበር ተምስሌት ተብላ ትታወቅ የነበረች አገር አሁን ከነሶርያ በልጣ ሚልዮኖች ዜጎች የሚፈናቀሉባት ዜጎች በመንጋ ውሳኔ በጠራራ ፀሃይ በኣደባባይ የሚገደሉባት የቀውስ ማሳያ ኣገር ከሆነች ቆይታለች ፡፡ 

ኣሁን አገራችን የገባችበት ከፍትኛ ቀውስ መነሻው በአዴፓ ኣስተባባሪነት በስመ ለውጥ ከውጭም ከውስጥም ለኣመታት የተገነባው ህገ መንግስታዊ ስርኣት ለማፍረስ የተሰባበሰቡ የትምክህት ሃይሎች በኣንድ ጎራ በማሰለፍ ትናንት የተደመሰሰውን የደርግ ስርኣት ያራምደው የነበረ ኣሃዳዊ ስርኣት ለማሰመለስ የያዘውን አላማ ለማሳካት መሆኑ ራሱም በተለያየ መድረክ ግልፅ አድርጎታል ፡፡  የዚህ ፀረ ህዝብ ድረጅት አላማ እንደሚታወቀው የትናንቱ የደርግ መፈክሮች በማንገብ ኣንድ አገር: ኣንድ ፓርቲ: ኣንድ ቋንቋ: በኣጠቃላይ የኣማራን ልዕልና እናረጋገጣለን የሚል  ስትራተጂ በመከተል ይሳካለት ኣይሳካለት ሌላ ጉዳይ ሆኖ በነዚህ ትናንት ተሞክሮው የወደቁ አስተሳሰቦችን ኣሁን ኣዲስ ቀለም ቀብቶ በግልፅ በማራመድ ኣገሪቱን ላማፈረስ ከፍተኛ ሚና በመጫወት ላይ ይገኛል ፡፡ 

ይህ ፀረ ህዝብና የትምክህተኞች ወኪል የሆነ ድረጅት በተለይ በኣሁኑ ሰኣት በግልፅ እያራመዳው ያለው ኃላ ቀርና አገሪቱን የሚበትን ኣሰተሳሰብ የሚያራምድ የነበረ የደርግ ስርኣት በመደምሰስ ከፍተኛ ሚና የነበረው የትግራይ ህዝብና ድርጅት ሰም በማጥፋት ከዛ ኣልፎም ከቻለ ከሌሎች ግብረ አበሮቹ ጋር ተባበሮ ይህን ህዝብ ለማጥፋት የደርግን የጥፋት ዘመቻ ለመድገም ሌት ተቀን ሲታክት ይታያል ፡፡ ያው ከባለፈው ሁለት ሶስት ኣመታት ጀምሮም ይህን ኣላማ ለማሳካትም በተለይ በክልሉ ይኖሩ በነበሩ የትግራይ ተወላጆች ላይ ከ2008 ዓ/ም ጀምሮ ራሱ በሚቆጣጠረው የፀጥታ ሃየል ሳይቀር በማሰማራት በንፁሃን ዜጎች ብዙ በደልና ግፍ እንዲደርስ እንዳደረገ መላው የኢትዮጵያ ህዝብ በሚገባ የሚያውቀው ጉዳይ ነው  ፡፡ 

ስለዚህ አዴፓ አሁን በሚያራምደው ኣስተሳሰብና እየፈፀመው ያለው ተግባር ሲመዘን ይህ ድርጅት የስም ለውጥ ካልሆነ በስተቀር ትናት የደርግ ስርአት ይመራ የነበረው የቀይ ሽብር ተዋናይ የሆነው ኢሰፓ ፓርቲ በትግራይ ህዝብ ይፈፅመው የነበረ ግፍና በደል ኣሁንም በዚህ ድርጅት እየተደገመ እንዳለና ምንም ልዩነት እንደሌለ ከዚህ በላይ ማስረጃ ማቅረብ ኣያስፈልግም ፡፡ በዚህ መሰረት በተለይ የትግራይ ህዝብ እንደትናቱ የደርግን ስርኣት ለማሸነፍ ያደርግ የነበረውን ትግልና ትንቅንቅ ዳግም ደርግን ከተካ ከደርግ ምንም ልዩነት የሌለው የትምክህት ሃይል ወኪልና ቀንደኛ ኣንቀሳቃሽ የሆነ አዴፓ እንደገና የሚፋለምበት የተለየና ኣዲስ የትግል ምዕራፍ ላይ እንደገባ ኣውቆ እንደተለመደው በጠላቶቹ ላይ እንደትናነቱ ድል ለማስመዝገብ ከመሪ ድርጅቱ ህወሓት ጋር ተሰልፎ የሚፋለምበት ጊዜ አሁን መሆኑን ተገንዝቦ ኣስፈላጊውን ዝግጅት ከወዲሁ ማድረግ ይጠበቅበታል ፡፡

አይተ ፍስሃ !

አዴፓ የፈልገዉን አቆአም ቢወሰድ የህወሓት ድክመትን ያሳያል :; ህወሓት ፀረ ኢትዮጵያ የቆመ ድርጅት ነው ህወሓት ለምንድን ነው የኢትዮጵያን የቀይ ብህር ዳርቻ ሙሉበሙሉ ለኤርትራ አንዲሰጥ  ያደረገው? ህወህት መቼ ነው ለኢትዮጵያ የሚቆመው? ለ ትግራይ ሕዝብ አደፓ ለኢትዮጵያ አስከቆመ ድረስ እስፓ ሆነ አልሆነ ትርጉም የለውም :: የትግራይ ሕዝብ ለኢትዮጵያ ሕዝብ ከሚቆሙ ድርጅቶች ግን ተሰልፎ ይታገላል::