Thursday 3 January 2019

ዛሬም አሰብን እንላለን! በያዕቆብ ኃይለ ማርያም

ለክቡር ዶክተር አብይ አህመድ
የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚንስትር
አዲስ አበበ፤ ኢትዮጵያ፤

የአድህሮትና የክፍፍል በአንድ ጎራ፤ የነጻነትና የአንድነት ኃይሎች በሌላው ጎራ፤
ሰቅዞ፤ በያዛቸው ትግል ዉስጥ ሆነው፤በሚፋለሙበት በዚህ ተስፋ ሰጪ ወቅት፤የኢትዮጵያ የባሕር
በር ጥያቄ ዛሬ ማንሳት፤ዋናው የተጀመረዉ በጎ እንቅስቃሴ፤ ማዘናጋት እንዳይሆን የሚሰጉ ሰዎች
ይኖራሉ። ሆኖም የአሰብ ባለቤትነት ጥያቄ የአገር ሕልዉናና ልማት ጥያቄ አንዱ አካል
እንደመሆኑ መጠን፤ዛሬ በተከሰተዉ ብዙ ተስፋ ከጫረዉ የዲሞክራሲና የአንድነት እንቅስቃሴ ጋር
ተደምሮ ገና በጥዋት መነሳት ያለበት ጉዳይ ነዉ። የአሰብን ጥያቄ ግዙፍነት ተረድተዉ አዲሶቹ
የኢትዮጵያ መሪዎች በቅድሚያ አጀንዳቸዉ ዉስጥ እንዲያካትቱት በአክብሮት ለማሳሰብ ነዉ።
ዛሬ የተነሱት የኢትዮጵያ መሪዎች የኢትዮጵያን ጥቅሞችና መብቶች የሚያስከብሩ ናቸዉ የሚል
ፍንጭ ስለአየን ግዳዩን እንድናነሳ ቀሰቀሰን።

ኤርትራ ሕገ ወጥ በሆነ መንገድ ተገንጥላ፤ የኢትዮጵያን ሉዐላዊ ግዛት የነበረችዉን
አሰብን ስትይዝ፤አሰብ በታሪክ፤በሕግና በስነመንግሥት እሳቤ የኤርትራ አካል እንዳልነበረች
ለማስረዳት ኢትዮጵያዉያን ምሑራን ያልፈነቀሉት ድንጋይ፤ ያልማሱት ስር አልነበረም። በወቅቱ
አሰብ የኢትዮጵያ ግዛት ለመሆኗ ለማስረዳት ያህል ኢትዮጵያዊ ጉዳይ አልነበረም። የአገሪቱ
ፕሬዚደንት የነበሩት መቶ አለቃ ግርማ ወልደጊዮርጊስ የኢሓደግ ባለሥልጣናት አቶ መለስ
ዜናዊ፤ አቶ ኃይለማርያም ደሳለኝና አቶ በረከት ስመዖን ከመንገዳቸዉ ወጥተዉ፤ አሰብ
የኤርትራ ግዛት ነች፤ኢትዮጵያ በአሰብ ላይ ምንም መብት የላትም ሲሉ መስክረዋል። ይኸ ስም
ማጥፋት ሳይሆን በሰነድ ሊረጋገጥ የሚችል ጉዳይ ነዉ።

እ.አ.አ. በ2000 ዓ.ም. በኢትዮጵያና በኤርትራ መሃከል በተደረገዉ አላስፈላጊና
ትርጉም የለሽ ጦርነት በኢትዮጵያ ድል አድራጊነት እንደሚደመደም ግምት ተወስዶ ስለነነበረ፤
ጦርነቱ አልቆ ወደ ድርድር በሚኬድበት ጊዜ ለኢትዮጵያ ተደራዳሪዎች ግበዐት የሚሆኑ፤
በሕግና በታሪክ የተደገፉ ሃሳቦች፤ ምሁራን በተለያዩ ሚዲያ አቅርበዉ ነበር። ጦርነቱ
እንደተጠበቀዉ በኢትዮጵያ አሸናፊነት ሲደመደም ኢሕአደግ ከመነሻዉ፤ኤርትራን ለማስገንጠል
በብዙ የደከሙት የኢትዮጵያ ጠላት የአልጄሪያዉ ፕሬዚደንት ቡተፍሊካን አስታራቂ እንዲሆኑ
ጠየቀ። ቡተፍሊካም አቶ ኢሳያስን ና አቶ መለስን አጨባብጠው ዉዝግቡ ዓለም ሁሉ እምነቱ
ወደጣለበት ዓለም አቀፍ ፍርድ ቤት (International Court of Justice) ከመውሰድ ፈንታ በገንዘብ
በተገዙ ግለሰቦች እንዲዳኝ የድንበር ኮሚሽኑ ጉዳይ ወደዚያ ተመራ።

እዚህ ላይ አንድ አስገራሚ ምናልባትም በአገር ክሕደት ወንጀል የሚያስጠይቅ በደል
መጠቀስ አለበት። የድንበር ኮሚሽኑ ዳኞች የቀረበላቸውን ማስረጃዎች ተንተርሰዉ ጾረና
የኢትዮጵያ ግዛት መሆኗን ዉሳኔ በሚሰጡበት ጊዜ በኢትዮጵያ መንግሥት ተእዛዝ ኢትዮጵያን
የወከሉ ጠበቆች፣ “የለም ተሳስታችኋል፤ ጾረና የኤርትራ ግዛት ነዉ” ብለዉ በመከራከራቸዉ
ዳኞቹ ምርጫ በማጣት ጾረናን ወደ ኤርትራ አካለሉት።በታሪክና በሕግ ሥነ መንግሥት የተካኑ
ኢትዮጵያዉያን አገልግሎታቸዉን በነጻ እንደሚለግሱ ቢረጋገጥም፤ ኢሕአደግ ስለኢትዮጵያና
ኤርትራ ታሪካዊና ወቅታዊ ግንኙነት ምንም ዕዉቀት የሌላቸዉ ዳኞች በዘጠኝ ሚሊዮን ዶላር
ተቀጥረዉ፤ ጉዳዩ ወደነዚህ ዳኞች ችሎት ተመራ።

በክርክሩ ወቅት ኢትዮጵያን የወከሉ ጠበቆች በአቶ መለስ ተዕዛዝ መሆን ይኖርበታል፤ አንድም
ጊዜ አሰብ በክርክራቸዉ ዉስጥ አላነሱትም።ይልቅስ እጅግ በጣም አስገራሚ የሚሆነዉ ዉሳኔዉ
ጣሊያኖች በታላቁ መሪ በእምዬ ምኒልክ ላይ በግድ በተጫኑ ዉሎች ጣሊያን በኢትዮጵያ ላይ ጦር
በማዝመቷ፤ በተባበሩት መንግሥታት ኢትዮጵያም በአዋጁ ባሰረዘቻቸው ዉሎች ላይ በመመርኮዝ
ነዉ። እነዚህ ኢትዮጵያን የወከሉ ጠበቆች የተባበሩት መንግሥታት ጠቅላላ ጉባዔ በዉሳኔ ቁ፤
289(IV)የኢትዮጵያ ተገቢና ሕጋዊ የባሕር በር ባለቤትነት መብት ቢረጋገጥም ጠበቆቹ ከቁብ
ሳይቆጥሩት ታለፈ። በተጨማሪም ማንኛዉም መንግሥት ወይም አገር፤ ከሻቢያና ከኢሕአደግ
በስተቀር፤ኤርትራ የኢትዮጵያ ቅኝ ግዛት ነበረች ያለ የለም። “ሻቢያ ኤርትራ የኢትዮጵያ ቅኝ
ግዛት ነበረች” ካለ የሚያስከትለዉን ሕጋዊ ዉጤት መቀበል ነበረበት። ዛሬ የልማዳዊ ሕግ
(Customary law) አካል የሆነዉ የአፍሪካ አንድነት ድርጅት ጠቅላላ ጉባዔ በካይሮ ስብሰባዉ
በዉሳኔ ቁ. AHG/Res 61(1) ያሳለፈዉ የሕግ መርሕ፤አንድ በቅኝ ግዛትነት የተገዛ አገር፤ ነጻ
በሚወጣበት ጊዜ ቅኝ ግዛት በነበረበት ወቅት የነበረዉ ድንበር ማክበር ይኖርበታል፤ በማለት
ደንግጓል።ይህ መርሕ “በያዝከዉ እርጋ (Uti possedetis) የሚል ድንጋጌ ነዉ። ኤርትራ “ነፃ”
በወጣችበት ጊዜ፤ አሰብ እራስ ገዝ የኢትዮጵያ አካል ስለነበረች፤ኤርትራ ነፃ ስትወጣ፤ አሰብ
በኢትዮጵያ እጅ መቅረት ነበረባት። ኢትዮጵያን የወከሉ ጠበቆች ይህንን መርሕና ሌሎችንም
ኢትዮጵያን የሚደግፉ የሕግ መርሆች ሳያነሱ ኮሚሽኑ ዉሳኔዉን ሰጠ። በዚህም ዉሳኔ ባድመንና
ጾረናን ሌሎችንም ለኤርትራ ሰጥቶ፤ በእግር መንገድ እርቀት፤ ሁለት ወደቦች የነበሯት
ኢትዮጵያ የባሕር በር ተዘግቶባት፤ ከቀይ ባሕር አካባቢ ተገልላ ቀይ ባሕርም የአረብ ሃይቅ ሆነ።
የድንበር ኮሚሽኑ በወረቀት ላይ፤ የማካለል ሥራ ከሠራ በኋላ ብዙም ሳይቆይ፤ በስምምነቱ
መሠረት ኮሚሽኑ መሬት እረግጦ በወሰኖቹ ላይ ችካል መትከል ነበረበት። ሆኖም አቶ ኢሳያስ
በኤርትራ ተሰማርቶ የነበረዉን የተባበሩት መንግሥታት የሰላም አስከባሪ ጦር በማባረራቸዉ፤
የድንበር ኮሚሽኑ፤ ከስምምነቱ ዉጭ፤ ወሰኑን በአየር አካልዬ የማስመሰል ችካል ተክያለሁ፡
(Virtual demarcation ) አድርጌአለሁ።” ብሎ አካባቢዉን ጥሎ እብስ አለ። ይህ ማለት እንግዲህ
የኢትዮጵያና የኤርትራ የማካለል ዉል የሚጥስ በመሆኑ ተካልሏል ማለት አይቻልም። ኤርትራ
ግን መካለሉ ተጠናቋል በሚል፤ኢትዮጵያ የያዘችዉን ግዛቶች፤ በተለይም ባድመን ኢትዮጵያ
እንድታስረክባት ለዓለሙ ሕብረተሰብ አቤቱታ ስታሰማ ቆታለች።

ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር!

በአሁኑ ጊዜ ከኢትዮጵያ የባሕር በር ጥያቄ ያመዘነ አገራዊ ጉዳይ ማሰብ አዳጋች ነዉ። ስለሆነም
አዲሱ ተስፋ እንድንሰንቅ ያደረገን የኢትዮጵያ መንግሥት አመራር ከኤርትራ ጋር ሁሉን አቀፍ
ድርድር ማድረግ ይጠበቅበታል። ድርድሩ ባለፈዉ እንደነበረዉ በብልጠትና በመሸዋወድ
የተጀነጀነ ሳይሆን፤ ጠቃሚነቱን አጉልቶ በማሳየት መከናወን አለበት። ምናልባትም ኤርትራን
ሊያማልሉ የሚትሉ ነገሮችን ማመልከትም ያስፈልጋል። አንድ ነገር ግን ግልጽ መሆን አለበት።
የድርድሩ አልፋና ኦሜጋ፤ አሰብን ወደ ኢትዮጵያ ማጠፍ መሆኑ ዉልፊት የማይባልበት
የመጨረሻ አቋም መሆን አለበት። ግልጽ ለመሆን ያህል፤ የአሰብ ወደብ በነፃ መጠቀም ማለትም
እንዳልሆነ ልብ ማለት ይገባል። ይህም ሲባል አሁን መገለጽ የማይገባቸዉ የኢትዮጵያን የአሰብ
ባለቤትነት ሊያስረግጡ የሚችሉ እርምጃዎችም ሊኖሩ ይችላሉ።
ክቡርነትዎ፤ለዚህ ጉዳይ ፍጹም የሆነ ትኩረት እንደሚሰጡት ተስፋ እያደረግሁ፤ ጽሑፌን በዚህ
እዘጋለሁ።
__________________________________

ኤርትራ ከ"መረብ-ምላሽ " ያለው አካባብ ስለመሆኑ የ "ዉጫሌ ስምምነት " በማያሻማ መንግድ ያሳያል:: "ኤርትራ" ከኢትዮጵያ ለ"ጣልያን" የተሰጠች ግዛት ናት ::  ስለሆነም በ ዉጫሌ  ስምምነት መሰረት  የኢትዮጵያና የኤርትራ ድንበር መካለል አለበት ::


Treaty of Wuchale (or, Treaty of Ucciale; in Italian, Trattato di Uccialli) was a treaty signed by King Menelik II of Shewa, later the Emperor of Ethiopia with Count Pietro Antonelli of Italy in the town of Wuchale, Ethiopia, on 2 May 1889. The treaty stated that the regions of Bogos, Hamasien, Akkele Guzay, and Serae were part of the Italian colony of Eritrea and is the origin of the Italian colony and modern state of Eritrea. Per the Treaty, Italy promised financial assistance and military supplies.
The contents of Article 3 of the treaty state the following: [1]
Art. 3. To remove any ambiguity about the limits of the territories over which the two Contracting Parties shall exercise the rights of sovereignty, a special committee composed of two Italian delegates and two Ethiopians will trace on the ground with appropriate signs a permanent boundary line whose benchmarks are established as follows:

a) The line of the plateau will mark the Italian-Ethiopian border;

b) Starting from the region Arafali, Halai, Saganeiti and Asmara are villages in the Italian border;

c) Adi Adi Nefas and Joannes will be on the side of Bogos in the Italian border;

d) From Adi Joannes a straight line extended from east to west will mark the border between Italy and Ethiopia.

Disputes over Article 17 regarding the conduct of foreign affairs led to the First Italo–Ethiopian War. The Italian version stated that Ethiopia was obliged to conduct all foreign affairs through Italian authorities, in effect making Ethiopia an Italian protectorate, while the Amharic version gave Ethiopia considerable autonomy, with the option of communicating with third powers through the Italians.[2] The misunderstanding, according to the Italians, was due to the mistranslation of a verb, which formed a permissive clause in Amharic and a mandatory one in Italian.[3]

Notes









  • TREATY OF WUCHALE UMBERTO I BY THE GRACE OF GOD AND THE WILL OF THE COUNTRY KING OF ITALY








  • Discussions include Chris Prouty, Empress Taytu and Menilek II (Trenton, NJ: The Red Sea Press, 1986), pp. 70-99; Marcus G. Harold, The Life and Times of Menelik II: Ethiopia 1844-1913 (Trenton: The Red Sea Press, 1995), pp. 111–134; and Hatem Elliesie, Amharisch als diplomatische Sprache im Völkervertragsrecht, Aethiopica (International Journal of Ethiopian and Eritrean Studies), 11, (Wiesbaden: Harrassowitz, 2008), pp. 235-244.

    _____________________________

    አ ፖ (AP) notes

     Ethiopia is part of the Red Sea. Land locking Ethiopia is unacceptable. Ethiopian politicians should address the question of the Mereb Melash (መረብ ምላሽ ), which should be part of Ethiopia. Ethiopia has a population of 110 million which would be 250million in 2060. It is injustice on Ethiopians in general that they are denied to use their own ports -Massawa and Assab. The problem has been TPLF, which gave away the Mereb Melash to Shaebia(Eritrea) and Egypt. We should reverse such decision made by Egypt and UN to land lock Ethiopia. We do not need Eritreans to join Ethiopia as we have people who stand for Ethiopia from birth to their death. Eritreans can never be Ethiopians. They are anti-Ethiopia. We should not allow  them to come to Ethiopia to exploit the resources we have. We are not Samaritans, hoping to go to heaven by our good deeds. We have millions of hungry people, which need to be supported. Let Eritreans solve they are own problems. We do not need Eritrea. We do not want Eritrea to unite with Ethiopia. We rather make good relations with Sudan, Kenya, Djibouti, Egypt etc. Eritrea and Eritreans should be treated as foreigners and should not get special treatment. They should be treated as we treat other Africans. Ethiopians should not beg Eritrea to get their own ports. We can have the South Mereb region based on the Wuchale Treaty and our politicians should demand the return of the South Mereb Region to Ethiopia. The boundary between Eritrea and Ethiopia should be delimited based on the Wuchale Treaty. The future international boundary  of Ethiopia and Eritrea would be like the map below (according  to the Wuchale Treaty).



    No comments: