Wednesday 19 December 2018

ሰው የለም ወይ?

ከተክለሚካኤል ኪ/ማርያም

በዚህ ዓለም በስመ ሰላም የማይሰራ ጉድ እንደሌለ በርካታ ፀሓፊዎችና ተማራማሪዎች በተደጋጋሚ ኣትተውታል፡፡አሁንም ቢሆን ሁኔታው እየባሰ እንጂ አየተሻሻለ እንደልሆነ በአገራችን በተጨባጭ እየታየ ያለ ጉዳይ ይመስለኛል፡፡እኛ ኢትዮጵያውያን ቆም በሎ ማሰብ ሲያቅተን ነው እንጂ ለዘመናት ያዳበርናቸውን የጋራ እሴቶቻችን በመናድና መለካም ገፅታችንን በማጠልሸት ላይ ስንሆን በተለይ በኣንዳንድ የፖለቲካ መሪዎች እየታዩ ያሉ ኣፍራሽ ተልኮዎች ጫፍ ላይ ደርሰዋል ቢባል ማጋነን ኣይሆንም፡፡እነዚህ የፖለቲካ ቡዱኖች የህዝቡ ክብርና አገሪቱ የምትተዳደርበትን ህገ መንግስት ወደ ጎን በመተው በስመ መገናኛ ብዙሃን በተደራጁ ኣንዳንድ ሚዲያዎች ፊታውራሪነት ህዝብ በህዝብ ላይ እንዲነሳ በማድረግ ላይ ናቸው፡፡

የዚህ ዓይነቱ ኣባዜ በስመ ኣማራ በተደራጁ ፓርቲዎች የባሰባቸው ሲሆን ኣማራን ያህል ታላቅ ታሪክ ያለውና የራሱ ስብእና ኣረጋግጦ ያደረ ህዝብ ምንም እንደማያውቅ በመቁጥር የዘርህ ህልውና ሊያጠፉት ተነስተዋል በማለት ኣልሰማቸውም እንጂ በትግራይ ላይ እንዲነሳ ነጋ ጠባ ሲወተውቱት ይሰማል፡፡የዚህ ዓይነት ስልት እስከ ቅርብ ጊዜ በኣማራ ቴለቪዥንና ሊሂቃን ወይ ፖለቲከኞች እየተባሉ ለአማራ ህዝብ ተቆርቋሪ መስለው በሚነቀሳቀሱ ተወስኖ ቢቆይም በዚሁ ሁለት ወራት ግን በፌደራል ደረጃም ቀዳሚ ኣጀንዳ ሆኗል፡፡

እዚህ ላይ የአማራ ህዝብ ማስተዋል ያለበት ቀደም ሲል ከኣክሱም እስከ ጎንደር ዘመነ መንግስት ያለው የአብሮነት ታሪክ ብሎም በአፄ ዮሐንስ ጊዜ የጎንደር ወንድም ህዝብንና ኣብያተ ክርስቲያናትን ለመታደግ ሲሉ የትግራይ ጀግኖች ከአማራ ጀግኖች ጋር አብረው መስዋእት በመክፈል በአንድ ጉድጓድ የተቀበሩበት የትናት ታሪክ እየተካደ መሆኑን ነው፡፡ መካድ ብቻም ሳይሆን ፋኖ ብለው ለስልጣናቸው መስዋእትነት እንዲሆኑ ባደራጁዋቸው ቡዱኖች ኣማካይነት የትግራይ ተወላጅ እንዲገደል ፣ ንብረቱ እንዲዘረፍና እንዲቃጠል አድርገዋል፡፡አሁንም እነዚህ በአማራ ስም የተደራጁ ፓርቲዎች ለቀጣይ ጥፋት በዝግጅት ላይ መሆናቸውን የኣማራ በተለየ ፣ የኢትዮጵያ ህዝብ ደግሞ በአጠቃላይ ልብ ሊለው ይገባል፡፡

የኢተዮጵያ ህዝብ ሲከታተለው እንደቀየ በአዴፓ የሚመራ የክልሉ መንግስት የፀጥታ ኣከላት ሳይቀሩ የሰው በጎችና እህል ሲዘርፉ ለአማራ ህዝብ አንገትን ያስደፋ ቢሆንም የክልሉና የፌዴራል መንግስታት ግን ግድያውንና ዘረፋው ሊያቆሙት ቀርቶ ሊያወግዙትም አልወደዱም፡፡ የትግራይ ህዝብም እንዲህ ለመሰለው እኩይ ተግባር በትእግስት ቢያልፈውም መልእክቱ ግን በሚገባ ተገንዝቦታል፡፡

ይኸውም እነዚህ በውጭና በውስጥ መሰርይ ሃይሎች ተገፋፍተው የሰከሩ ፖለቲከኞችና መንጋዎች እንቅስቃሴኣቸው ነገ እንደማይኖር ፣ ህዝቡ ግን ተለያይቶ እንደማይለያይ ሰለሚያውቅና ህዝብ የሚባል ጠላትም እንደሌለው ኣበክሮ ስለሚገነዘብ ነው፡፡

በሌላ በኩል «እንኳን ሲሸጡን ሲያስማሙንም እናውቃለ» ኣለች ፍየል እንደሚባለው ምን እንደ ተፈለገም የትግራይ ህዝብ በማያሻማ መልኩ ተገንዝቦታል፡፡እንዲሁም የሰው ኃይል ብዛት እያወራረዱ ቢውሉም «እይድህን ንጉስ በብዝኀ ሰራዊቱ» የሚለውን የነብዩ ዳዊት ክፍለ ንባብ ቢዳስሱት ህዝቡም ሆነ እነሱ ከጥፋት ማዳን ስለሚቻል ቆም ብሎ ለማሰብ አሁንም ጊዜው ኣልመሸም ስንል እነሱ እንደሚሉት የተፈለገውን ከበባ ቢደረግም ለህልውና ሌላ ኣማራጭ የሌለው መሆኑን የትግራይ ህዝብ ኣበክሮ ስለሚያውቅ የተጠነሰሰበትን የጥፋት ተንኮል እንደ አመጣጡ ከመመከት ወደ ኋላ እንደማይል የኢትዮጵያ ህዝብ እንዲገነዘብለት ይፈልጋል፡፡ 

እነዚህ ህግ የመይመለከታቸው የሚመስሉ ቱባ መሪዎች ቆም ብለው እንዳያስቡ ልቡናቸው ተሰውሮ ነው እንጂ ላለፉት 27 ዓመታት የተሰራ ልማቶትም ሆነ ጥፋት ለማን እንደሚመለከት የኢተዮጵያ ህዝብ በሚገባ ያውቃል፡፡በተለያዩ የቴለቪዥን መስኮቶች ተበዳዮችን በማቅረብ በትግርኛ ተናጋሪዎች ብቻ የተፈፀሙ በማሰመሰል እንዲናገሩ ቢደረግም እያንዳንዳቸው የተመረመሩበት ሰነድ በየደረጃው በሚገኙ የፖሊስ ምርመራ ክፍሎች እንዳሉና ፍፁም እንደማይገናኝ አንዳንድ ምንጮች ማረጋገጥ ጀምረዋል፡፡

ጤናማ ቢሆን ኖሮ ጉዳት የደረሰባቸው ወገኖች በኢሕአደግ ጊዜ ሲሆን አሁንም ራሱ በመምራት ላይ ስለለ ተበዳዮችን በተገቢው መካስና በዳዮችም ተመጣጠኝ ቅጣት እንዲየገኙ ማድረግ እንጂ ኣንድን ህዝብ በሌላው ላይ ጥላቻ በሚያሳድር መልኩ በተመሳሳይ ሰዓት በአራት ሚዲያዎች መተላለፉ አገራችንን ወደ ባሰ ኣለመረጋጋት  ሊወስዳት ካልሆነ ለኢትዮጵያ ህዝብም ሆነ ለተበዳዮቹ የሚፈይደው ነገር የለም፡፡

ይህ የጥፋት ዘመቻ ኣሁንም ተጠናክሮ እየቀጠለ ሲሆን በተለይ በአማራ ክልል ባለስልጣኖች በተከታታይ እየተረጨ ያለው የዘረኝነትና የፅንፈኛ ብሄርተኝነት መርዝ ስር እየሰደደ እንጂ እየተሲሻሻል እንዳልሆነ ሰሞንን በሰላም ኮንፈረንስ ስም ጎንደር ላይ እየተላለፈ የሰነበተው የጥፋት ፕሮፖጋዳ ለኣማረ ደህንነት ይበጃል ከተባለ ውጤቱ በቀጣይ የሚታይ ይሆናል፡፡

የተከበሩ ብርጋዴር ጀኔራል ኣሳምነው ፅጌ የሰላም ኮንፈረንስ ብለው ዘረኝነታቸውን በግልፅ ሲያራምዱ ያልተገነዘቡት ነገር እንደ ነበረ ግን እርግጠኛ ነኝ፡፡ይኸውም ወያኔ ውሰጣችን ገብቶ እየበታተን ነው ሲሉ በአንድ በኩል ሃላፊነታቸውን እንደልተወጡ እያረጋገጡ ሲሆን በሌላ በኩል ደግሞ በዚህ የቴክኖሎጂ ዘመን ከእርሳቸው ሌላ ትግራይን የሚያውቅ ሰው እንደሌለ ኣስበው በኣውሮፓ የሌሉ ህንፃዎች በትግራይ ተገንብተዋል ብለው መናገር ምን ያህል ግብዝነት እንዳለቸውና ታማኝነታቸውን በገዛ ራሳቸው እየሸረሸሩት እንደሆነ የበርካታ የኮነፈረንሱ ተካፋዮችና የኢትዮጵያ ህዝብ ትዝብት እንደሚሆን ኣልጠራጠርም፡፡

ቢቀበሉትም ባይቀበሉትም ለክብርነትዎና ለቡዱንዎ ግልፅ እንዲሆን የሚፈለገው የትግራይ ህዝብ ለኣማረ ሰፊው ህዝብ ክብር ስላለው የጥፋት ወከባችሁን ኣስወግዳችሁ የሁለቱ ክልሎች ህዝብ ተቀራርቦ በመነጋገር ችግሩ እናንተ የፈጠራችሁት ቢሆንም በተለመደውና ከኣያት ቅድመ ኣያት በወረሰው ኢትዮጵያዊ ጥበብ የመፍታት ችሎታው ኣሁንም ህያው ስለሆነ እድሉ ለሁለቱም ህዝብ ቢሰጥ ይበጃል፡፡ይህንን ሳይሆን ቀርቶ ወጣቱን ገፋፈታችሁ ወደ ግጭት ከገባ ግን መጨረሻ የሌለው ጥፋት ይፈፀማል፡፡ከታሪክ ተጠያቅነትም የሚመልጥ ሰው ኣይኖርም፡፡

ሌላ መነሳት ያለበት እንደ አውሮፓ አቆጣጠር በ1967 ዓ.ም እስራኤል ከምድረ ገፅ እንድትጠፋ ታቅዶ በዓረብ አገሮች በተከበበችበት ጊዜ ኣንድም ሉዓላውነቷ ታውቆ የምትኖር እስራአል ማረጋገጥ ፣ ኣለበለዚያ በስደት ተበታትኖ የሚባል የእስራኤላውያን ህልውና ያከትማል ብለው ቆርጠው በመነሳት ችግሩ በአሸናፊነት እንደተወጡ ታሪክ ያረጋግጣል፡፡

ኣሁንም ትግራይ በፌደራል መንግስቱ ያላት ተመጣጣኝ ውክልናና ተጠቃሚነት የተረጋገጠባት ክልል ሆና የምትቀጥል እንጂ ማንንም እንደፈለገ ጣቱ የሚቀስርባት ትግራይ ማየት የሚፈልግ ኣንድም ሰው ስለሌለ ምርጫው ኣንድ ሲሆን ለሰላም ጠንክሮ መስራትና በህልውናው ላይ የሚቃጣ ሁሉ መመከት ነው፡፡

እንዲህ ሊሆን የሚችለውም እኛ የፌደራላዊት ኢትዮጵያ ጠንካራ ምሰሶ እንሆናለን ስንል ሌሎች ብሄር ብሄረሰቦችም ተመሳሰይ ጥንካሬ ሳይኖራቸው የሚታሰብ ሰለማይሆን የሁሉም ክልሎች ጥንካሬ በጋራ ይገነባል፡፡በውስጥና በውጭ የቤት ስራ የተጠመዱ ፖለቲከኞች እንደሚሉ ሳይሆንም ኢትዮጵያና ኢትዮጵያነታችንም እንደ ነበረ ፣ ኣሁንም እንዳለ ለወደፊትም ህያው ሆኖ ይኖራል፡፡
 
 
 

No comments: