Sunday 9 December 2018

ኢትዮጵያ - የግብፆች የትያትር አደራሽ

ዳንሾ ሄሮን

ኢትዮጵያ የትያትር አደራሽ ከሆነች ፤ ተዋናዩስ ማነው? የትያትሩ ደራሲስ ማነው? ዳሪክተሩስ? ወዘተ ብላችሁ ትጠይቁኝ ይሆናል። ወደ ዋናው ሃሳቤ ከመግባቴ በፊት ለዚህ መልስ መስጠት ሳይኖርብኝ አይቀርም። እናማ መልሱ እንድህ ነው። የተውነቱ ደራሲዎች ግብፆች ናቸው። የተውነቱም ዳረክተሮች ግብፆች ናቸው። የተውነቱ ተጫዎዋቾች ደግሞ ኢትዮጵያዊያን ይሆናሉ ማለት ነው። የሚያሳዝነው ነገር ግን የተውኔቱ ተጫዋቾች ኢትዮጳዊያን ግብዞች የተሰጣቸውን ጨዋታ በስሜት እየነጎዱ ከመጫወት ውጪ የደራሲው ይሁን የዳሪክተሩ ማንነት ለማወቅና በትክክል ለመረዳት አቅምና ፍላጎት ያላቸው አይመስሉም። ተዋናዮቹ ይጫወታሉ፤ ይተራመሳሉ፤ አንዱ ገዳይ አንዱ ተገዳይ፤ አንዱ አሳዳጅ አንዱ ተሳዳች፤ አንዱ ሃቀኛ አንዱ ሌባ፤ አንዱ ፈጣሪ አንዱ ተፈጣሪ፤ ወዘተ በመሆን አደራሹ ያተራምሱታል። የተውነቱ ደራሲዎች የሆኑ ግብፆች ደግሞ፤ ድርሰታቸው መሬት ላይ ወርዶ ለተውኔት ስለበቃ ውስጣቸው በደስታና በትስፍህት ተመልቶ ልባቸው ቅቤ ጠጥተዋል። 
ይህ ኢትዮጵያን ወደ ትያትር አደራሽ በመቀየር የህዝቦችዋን ተውኔት እየተመለከቱ ከአባይ ማዶ ላይ ተዝናንተው ቁጭ በማለት የመዝናናት ልምዳቸው አንድ ሺ ዓመት ሳያስቆጥር አይቀርም። ላለፉት 27 ዓመታት ግን ይህን ልምዳቸው ስለተቋረጠባቸው ብዙ ታግለውና ደክመው፤ ገንዘብና ጉልበታቸው አባክነው፤ በአሁኑ ጊዜ ወደ ነበረበት ቢመልሱትም ጭንቀት ቢጤ ሳይዛቸውና የሞራል መላሸቅ ሳይደርስባቸው ግን አልቀረም። በመጨረሻ ግን የመሳካቱ አዝማምያ እየተገነዘቡ ስለሆነ ድካማቸው ከንቱ እንዳይቀር እየተጉበት ይገኛሉ። 
 

መግብያው ልብ ላለው ሰው ጥሩ መንደርደርያ ይሆነናል ብየ እየገመትኩ በኔ እምነት ኢትዮጵያ ባለፉት 27 ዓመታት ብዙ አመርቂ ውጤት ያስመዘገበችበትና ከአንድ ሚሊነም እንቅልፍ በኋል ባንና ከፍተኛ የኢኮኖሚ እምርታ ያሳየችበት ጊዜ ነው። በጤና ዘርፍ፣ በትምህርት ዘርፍ፣ በትራንስፖርትና መገናኛ ዘርፍ፣ በኤሌትርክ ኃይል ማመንጫ ዘርፍ ወዘተ ከፍተኛ ውጤት አስመዝግባለች። ህዝቦች ንቃተህልናቸው በተወሰነ ደረጃ ዳብሮ የልማትና የሰላም የዴሞክራሲ ፍላጎታቸው እየሰፋ የመጣበት ጊዜ ነበር። ይህ ያለፉት 27 ዓመታት የሚያካትተው ጊዜ የቆሻሻና የጨለማ ጊዜ ሳይሆን ኢትዮጵያ ከዘመናት በኋላ የብርሃንና የተስፋ ጭላንጭል ያየችበት፣ ህዝቦች በማንነታቸው ተከብረውና ዕውቅናቸው ተጎናፅፈው አከባቢያቸው ማልማት የጀመሩበት፣ የፌዴራሊዝም ስርዓትን በማነፅ በመፈቃቀድ እንዴት አብሮ መኖር እንደሚቻል ያሳዩበት ጊዜ ነበር።

ይህ ይሆን ዘንድ ህዝቦች ከፍተኛ መስዋእት ከፍለዋል። በዚህ ረገድ ተጠቃሽ የሆነ የተጋድሎ ታሪክ የፈፀመው የትግራይ ህዝብ አንዱ ነበር። በግልፅ መናገር ያለብን ጉዳይ የትግራይ ህዝብ መተክያ የሌለው ከፍተኛ መስዋእት ከፍለዋል። የትግራይ ህዝብ መስዋዕት በጦር ግንባር ላይ በተሰው ጀግኖች፣ በራሽያ ሰራሹ የደርግ አውሮፕላኖችና መድፎች የተደበደብ ሰላማዊ ህዝብና የወደመ ንብረት ብቻም አይገለጥም። ከድል በኋል የተከፈለ፤ እስከ አሁንም እየተከፈለ ያለ መስዋዕት ስፍር ቁጥር የለውም። የአማራ ሊህቃንና የአማራ ገዢ መደቦች ምንም ዓይነት ዕውቅና ባይሰጡትም አንዳንድ እውነታዎች ልግለፅ። (በዚህ አጋጣሚ ከአማራ ህዝብ ሙግት እንደሌለኝ ለማሳወቅ ወዳለሁኝ። ሙጉቴ ከአማራ ሊህቃንና ገዢ መደቦች ነው።)
ከተከፈሉት መስዋዕቶች ታጋዮች ያጫወቱኝ አንዳንድ እውነታዎች ላጋራችሁ። በሽግግሩ ወቅት በኢህአዴግ ከተከናወኑ አስደናቂ ፍፃሜዎች አንዱ ሰላምና መረጋጋት መፍጠር ነበር። ለዚህ ሲባል ለታጋዮች የወረደ መመርያ “ቢተኮስብህም አትተኩስ!” የሚል ነበረ። ትርጉሙ ግልፅ ነው። ከነሙሉ ትጥቅህ፤ ከነሙሉ ጀግንነትህ ቢተኮስብህም አትተኩስ። ይልቁንስ ለኢትዮጵያ ህዝብ ሰላምና መረጋጋት ስትል ደረትህን ለጥይት ስጥና መስዋዕት ሁን ማለት ነበረ። ጉዳዩም በመመርያው መሰረት ተፈፀመ። ይህም ከትግራይ ህዝብ አብራክ የፈለቁ የህወሓት ታጋዮች የጠነከረ ዲሲፕልን መገለጫ ነበረ። በዚህ መስዋዕት ምክንያት ያለ ምንም የተጋነነ ችግር ኢትዮጵያ በሰላም ተሸጋገረች። በሚሊየኖች ይቅርና በሽዎች የሚቆጠሩ እንኳ በገዛ አገራቸው የተፈናቀሉ አልነበሩም። በዚህ መስዋዕት ምክንያት ህፃናትም አልታረዱም ፤ ንፁሃን ዜጎችም በጠራራ ፀሃይ ላይ በድንጋይና በብረት ተወግረው አልተገደሉም። 

ሌላው መስዋእት የተከፈለበት ጉዳይ ህገ መንግስታዊ ስርዓቱ ከፀደቀ በኋላ ለሚኖረው መከላከያ ሰራዊት የተመጣጠነ ይሆን ዘንድ የህወሓት ታጋዮች መቀነስና ከማዕረጋቸው አንድ ደረጃ እንድወርዱ ማድረግ ነበር። ከፍተኛ ተጋድሎ ፈፅሞ አምባገነን ስርአት የገረሰሰ ታጋይ በ 3 እና 5 ሺ ብር ድጎማ ተሰናበተ። በተጨማርም በጀግንነቱ፣ በፈፀማቸው አኩሪ ተግባራት የተጎናፀፈውም ወታደራዊ ማዕረግ ለማረካቸው የደርግ ወታደሮች ለነ ከማል ገልቱና አሳምነው ፀጌ ማስተላለፍ ግድ ሆነበት። ጦርነት ሲመጣ አ
ት ምራን ይሉ ነበር። ሰላም ሲመጣ ደግሞ እኛ እንምራችሁ ይላሉ።

በተቃራኒው ገና ኢህአዴግ አዲስ አበባ ሲረግጥ፤ የአማራ ሊህቃንና ገዢ መደቦች በትግራይ ህዝብ ላይ የፈፀሙት የታንክና የአውሮፕላን ድብደባቸው ቅስም ሲሰበረ ፤ ሌላ የትግራይ ህዝብ የሚደበድቡበት መሳርያ አዘጋጁ። ከፍተኛ የሆነ የብዕር ዘመቻ ከፈቱበት። በግነትና በውሸት ድርሰት የተካኑ የአማራ ሊህቃን ትግራይ በሃብት ልትሰምጥ ነው እያሉ ለ27 ዓመታት ሰበኩ። ዳሩ ግን ኢትዮጵያ ከድህነት ወለል ያለ ህዝብዋ 23% ሲሆን ፤ በሃብት የተንበሸበሸችው ትግራይ ደግሞ ከድህነት ወለል ያለ ህዝብዋ 29% ሆነ። አውቆ የተኛ ቢቀሰቅሱት አይሰማምና የውሸት ዘመቻቸው በበለጠ እያጦዙት ይገኛሉ። ከአባይ ማዶ የሚላክላቸው የገንዘብ ምንጭ ደግሞ ኢትዮጵያን ለማተራመስ ሲበትኑት ይታያሉ። በዚህ ገንዘብ ምክንያት ዜጎች ቢታረዱ፣ ሰላም ቢደፈርስ፤ ሚሊየኖች ቢፈናቀሉ ጉዳያቸው አይደለም። የትግራይ ህዝብ ለማዳከም ከማንኛውም ሰይጣን ይሁን ዲያብሎስ ከመተባበር በላይ አልፈው ይተጋሉ። በዚህ የአማራ ሊህቃን አስተሳሰብ ምክናያት ግብፆች ፈታ ብለው ይዝናናሉ።

ይህ አካሄድ (Pattern) ራሱ እየደገመ ያለ አካሄድ ይመስለኛል - ታሪክ ራሱን ሲደግም። በታሪክ ሂደት ውስጥ የአማራ ሊህቃንና ገዢ መደቦች በትግራይ ህዝብ ላይ ስፍር ቁጥር የሌለው ክህደት ፈፅመዋል። በአፄ ዮሃንስ ጊዜ የፈፀሙት ክህደት አሁን እየፈፀሙት ካለው ክህደት የባሰ
ነበር። አፄ ዮሃንስ የኢትዮጵያን ግዛት ለማስጠበቅና የባህር ወሰንዋ ለማስከበር ህዝባቸው አስተባብረው ከግብፅ፣ ከማህድስት፣ ከኢጣልያን ወዘተ ለዓመታት ሲፋለሙ አፄ ሚኒልክ ሁለተኛ መቼ ተባበርዋቸው? ጎንደር ሲትቃጠል አፄ ሚኒልክ ሁለተኛ ምን ሲፈይዱ ነበር? ስለእውነት ሊለምናችሁና አፄ ሚኒልክ ሁለተኛ አፄ ዮሃንስን ቢተባበሩ ኖሮ ምን ዓይነት ኢትዮጵያ ልትፈጠር እንደነበረ እስቲ ቆም ብላችሁ አስቡ። በሌላ መልኩ የኢትዮጵያ ህዝቦች በየፊናቸው ታግለው የገነቡት ፌደራል ስርዓት ለማፍረስ የአማራ ልህቃን ቢቆጠቡ ኖሮ የኢትዮጵያ ታላቅነት ወዴት እያማራ እንደነበር እስቲ ጭንቅላታችሁን መሰረት ከሌለው ጥላቻ ነፃ አድርጋችሁ ቆም ብላችሁ አስቡ። 

አንዳንድ ጊዜ የአማራ ሊህቃን ብሔራዊ ዕርቅ ይላሉ። የህዝብ ታሪክ እየሰረቅ፤ የህዝብ አስተዋፅኦ በጉልበት ፈልቅቀህ እየነጠክ፤ ህዝቦች በአፀያፊ ቃላት እየፈረጅክና በአደባባይ እየወረፍክ፤ እኔ የኢትዮጵያ ፈጣሪ ስለሆንኩ ህዝቦች የኔን የበላይነት ይቀበሉ ብለህ በአደባባይ እየሞገትክ፤ የሚኒልክን ፕሮጀክት አስቀጥላሎህ እያልክ በአደባባይ እየደሰኮርክ እንዴት ተብሎ ነው ብሔራዊ ዕርቅ የሚመጣው? ብሔራዊ ዕርቅ ማለትስ ህዝቦች በመፈቃቀድና በመከባበር በጋራ ጥቅም ላይ ተመርኩዘው ከሚመሰርቱት ፌደራል ስርዓት ውጭ ምን ዕርቅ ይኖራል? ወይስ ከ100 ሚልዮን በላይ የሆነ ህዝብ በአንድ አደራሽ ሰብስበው ማስታረቅ ይፈልጋሉ?

ኢትዮጵያ በዚህ ሁኔታ ከቀጠለች ህዝቦችዋ ለከፍተኛ እንግልት ይጋለጣሉ፣ ኢኮኖሚዋ ይላሽቃል፣ ከፍተኛ የሆነ የስራ እጦት ይበራከታል፣ የጦር አበጋዞችና አንጃዎች ይበራከታሉ፣ በዚሁም ምክንያት ስርዓት አልበኝነት ይበራከታል፣ ግብፆችም ተውኔቱን የመምራት አቅማቸው በበለጠ ያድጋል፣ ኢትዮጵያም ወደ መንግስት አልበኝነት ታመራለች (failed state)። ኢትዮጵያዊያን አመናችሁም አላመናችሁም ይህ እንዳይሆን በቁጥር አንድ አደብ መግዛት ያለባቸውና ቆም ብለው ማሰብ ያለባቸው የአማራ ሊህቃንና የአማራ ገዢ መደቦች ናቸው። በሁለተኛ ደረጃ ደግሞ ሌሎችም እንደዚሁ የድርሻቸው መወጣት አለባቸው። ይህ የማይሆን ከሆነ ከመተላለቅ ይልቅ ተፋቅሮው የተጋቡ ባልና ሚስት፤ ተፋቅረው መኖር ካልቻሉ፤ በፍቅር መለያየት ከሌሎች ሁሉም መንገዶች የተሻለ መንገድ እደሆነ ሁሉ በፍቅር ተለያይተን ብናየው የተሻለ ይመስለኛል።

No comments: