ከልኡል
ገብረመድህን
እውነት መቀበል ወንጀል ከመፈፀም በላቀ ይከብዳል ። ቅንነትና መልካም ምግባር የጎደለው ሰው ለእውነት አይኖርም ። ከእውነት የራቀ ሰው ሰሜታዊ ከመሆን አያልፍም። በሐሳብ ልዕልና አይመራም ። የሀሳብ ልዩነት አይቀበልም ። ከእውነት የራቀ ሰው ከራሱ አመለካከትና ዕይታ ውጭ የመኖር ውስጣዊም ሆነ ውጫዊ ቁመና የለውም ። የሁኔታዎች ክሰተት መነሻ ምክንያት አላቸው ። ያ መነሻ ምክንያት በእውነት ላይ የተመሰረተ ሊሆንም ላይሆን ሊችል ይችላል ። ተደጋጋሚ ሀሰት መቼም ቢሆን እውነት አይሆንም ። ነገር ግን ለአጭር ጊዜም ቢሆን የሚያስከትለው ማህበራዊ ጉዳት መኖሩ አይቀርም ይሆናል ። ምክንያቱም ሀሰት ( Falsification ) በራሱ ማህበራዊ ችግሮች የመፈልፈል አቅም አለው ።የማህበረሰብ ታሪክና ባህል ላይም ተፅዕኖ ይኖረዋል ። ለሚነሱ ማህበራዊ/ፖለቲካዊ / እንዲሁም ኢኮኖሚያዊ ችግሮች መነሻ ምክንያት የሚመረምር ማህበረሰብ በሌለበት ወይም ባልዳበረበት ሁኔታ ሀሰት ቦታ ያገኛል ። በተለይ ፖለቲካ የሀሰት ማጣፈጫ ቅመማ ቅመም (Fabrication ) ሲታከልበት የሚያስከትለው ማህበራዊ ቀውስ መገመት ያስቸግራል ። በተለይ እንደ ኢትዮጵያ ላሉት አገራት ያልተመጣጠነ እንዲሁም ያልተሰካከለ የፖለቲካና ኢኮኖሚ እድገት ላይ የሚኖሩ በመሆናቸው ለፖለቲካ ፕሮፖጋንዳ ተጋላጭ ናቸው ። ግልጽነት እንዲሁም ተጠያቂነት የሌለው የፖለቲካ ስረአትም ከእውነታ ውጭ የሚወራጭ ከመሆን አያልፍም ።
እውነት መቀበል ወንጀል ከመፈፀም በላቀ ይከብዳል ። ቅንነትና መልካም ምግባር የጎደለው ሰው ለእውነት አይኖርም ። ከእውነት የራቀ ሰው ሰሜታዊ ከመሆን አያልፍም። በሐሳብ ልዕልና አይመራም ። የሀሳብ ልዩነት አይቀበልም ። ከእውነት የራቀ ሰው ከራሱ አመለካከትና ዕይታ ውጭ የመኖር ውስጣዊም ሆነ ውጫዊ ቁመና የለውም ። የሁኔታዎች ክሰተት መነሻ ምክንያት አላቸው ። ያ መነሻ ምክንያት በእውነት ላይ የተመሰረተ ሊሆንም ላይሆን ሊችል ይችላል ። ተደጋጋሚ ሀሰት መቼም ቢሆን እውነት አይሆንም ። ነገር ግን ለአጭር ጊዜም ቢሆን የሚያስከትለው ማህበራዊ ጉዳት መኖሩ አይቀርም ይሆናል ። ምክንያቱም ሀሰት ( Falsification ) በራሱ ማህበራዊ ችግሮች የመፈልፈል አቅም አለው ።የማህበረሰብ ታሪክና ባህል ላይም ተፅዕኖ ይኖረዋል ። ለሚነሱ ማህበራዊ/ፖለቲካዊ / እንዲሁም ኢኮኖሚያዊ ችግሮች መነሻ ምክንያት የሚመረምር ማህበረሰብ በሌለበት ወይም ባልዳበረበት ሁኔታ ሀሰት ቦታ ያገኛል ። በተለይ ፖለቲካ የሀሰት ማጣፈጫ ቅመማ ቅመም (Fabrication ) ሲታከልበት የሚያስከትለው ማህበራዊ ቀውስ መገመት ያስቸግራል ። በተለይ እንደ ኢትዮጵያ ላሉት አገራት ያልተመጣጠነ እንዲሁም ያልተሰካከለ የፖለቲካና ኢኮኖሚ እድገት ላይ የሚኖሩ በመሆናቸው ለፖለቲካ ፕሮፖጋንዳ ተጋላጭ ናቸው ። ግልጽነት እንዲሁም ተጠያቂነት የሌለው የፖለቲካ ስረአትም ከእውነታ ውጭ የሚወራጭ ከመሆን አያልፍም ።
በኢትዮጵያ የሀሰት
እንጂ የእውነት ፖለቲካ
አልተለመደም ። የስሜት
እንጂ የምክንያት / rationality
/ ፖለቲካ በግልጽ አይታይም
፣ አይሰማም ። የጥላቻ
እንጂ የመከባበር ፖለቲካ
የለም ። የስልጣን ፍላጎትና
መግዛት እንጂ የማሰተዳደር
ፖለቲካ የለም ። የመንደርና
ብሔር ፖለቲካ እንጂ አንድነት
ላይ የሚሰራ ፖለቲካ / Politics
of National Unity / የለም ። የሀገር ሀብት
የሚመዘብር ፖለቲካ እንጂ
የአገር እድገት የሚያፋጥን
የፖለቲካ ሰርአት የለም
። ሰብዓዊ መብት ጣሸና
ረጋጭ እንጂ የዜጎች መብት
የሚያከብር አልያም የሚያስከብር
የመንግሥት አሰተዳደር
የለም ። የሐሰት ትያትር
በህዝብ ላይ የሚተውን
ስርአትና መንግሥት እንጂ
የህዝብና የአገር ደህንነት
የሚያስጠብቅ መንግስት
የለም ። በአጠቃላይ የኢትዮጵያ
የፖለቲካ ሰርአት ካንሰር
ነው ። የህዝብ ስርአትና
መንግሥት መመሰረት ጊዜ
የሚሰጠው ጉዳይ አይሆንም
።
በኢትዮጵያ የመንግስት
ሰርአት አሰተዳደር ሂደት
አበቅ የለህ የሆነ የመንግስት
አሰተዳደር የለም ። በንጉሡ
ዘመን ፊዳል ወይም ጭሰኛ
የሚሉ አሰልቺ አገላለጾች
ይነገሩ ነበር ። በደርግ
ሰርአት አድሀሪያን ወይም
ፀረ አብዮተኞች ፣ ተገንጣዮች
፣ ወንበዴዎች ፣ የፍየል
ወጠጤዎች ወዘተ የሚሉ
ተራ የፖለቲካ አባባሎች
ይነገሩ ነበር ። በኢህአዴግ
ሰርአተ ዘመንም ዝመና
አልታየም ።የደርግ ርዝራዠ
፣ ፀረ ልማት ፣ ፀረ ሰላም
፣ ፀረ ህዝብ ፣ ፀረ አገር፣
ፀረ ህገ መንግሰት የሚሉ
የበሰበሱ የመንግስት ፖለቲካ
አጠቃቀምና አሰራር የኢትዮጵያ
ህዝብ ሲያሸብሩ የቆዩ
እርባና ቢሰ / ዋጋ ዘይብሎም/
የድንቁርና አገላለፆች
ነበሩ ። ደግሞ የደርግ
ሰርአት ያገለገሉ የነበሩ
ኢሰፓዎች የኢህአዴግ ፀበል
ተነክሮ በኢህአዴግ ሰርአት
እሰከ ዶክትሬት ደረጃ
የደረሱም አሉ ። ኢህአዴግ
የተደራጀና የበቃ በደርግ
ሰርአት የነበረ የኢትዮጵያ
መከላከያ ሰራዊት መበተን
አልነበረበትም ። የአገር
አንድነት ስሜት ጉዳት
የጀመረውም ከደርግ ወታደር
ብተና ማግስት ጀምሮ ነው።
ሰውን የማሳነሰና የማግለል
የመንግሰት ፖለቲካ ተንኮሎችና
ሻጥሮች / Unethical government conspiracies / ከትውልድ
ትውልድ በቅብብሎሽ/
pattern / መልክ የመጡ ናቸው ።
መንግስት ህዝባዊ ትያትሮች
/ Movies / የሚሰራ ከሆነ የትያትር
ባለሞያዎች ምን ይሰሩ
?። የደህንነት ተቋም በዜጎች
ላይ ጭካኔ የተላበሰ ግፍና
ሰቆቃ የሚፈፀም ከሆነ
እንደ ተቋም መኖሩ ለምን
ያሰፈልጋል ?። የፖሊስ
ተቋም ያለ ፍርድ ቤት የመያዣ
ትዕዛዝ ተጠርጣሪዎች ከመንገድ
የሚያፍን ከሆነ የፖሊስ
ተቋም ለምን ያሰፈልጋል
?። የፍርድ ቤት ተቋም በህግ
የሚፈለግ ሰው በህግ ቁጥጥር
ሰር ከሆነ በኋላ በተጠርጣሪው
ግለሰብ ላይ መንግሰታዊ
ትያትር መሰራት ለምን
ያሰፈልጋል ?። የኢህአዴግ
ውልደትና ባህል ተምሮ
ያደጉ ጠቅላይ ሚኒስቴር
ዶክተር አብይ አህመድ
ካደጉበት የፖለቲካ ባህል
ለመላቀቅ ችግር ላይ ናቸው
። ለውጥ አደናቃፊዎች
፣ ጥቅማቸው የተነካ አድር
ባዮች ፣ የቀን ጅቦች ፣
ተላላኪዎች የሚሉ የልጠፋ
ስያሜዎች በጠቅላይ ሚኒስቴር
ዶክተር አብይ የሚገለፁ
የፖለቲካ ማጥቂያ ስሞች
መሰማት እንዴት እንደሚሰለች
ጠቅላይ ሚኒስትሩ ቢያውቁ
ባልተጠቀሙት ነበር ።
አንድ በሳል ፖለቲከኛ
በፖሊስና ሀሳብ ይሞግታል
እንጂ እንዴት ተራ ጉዳይ
ላይ ጊዜ ያጠፋል ! ።ይህ
የወረደ የግብዞች የማይጠቅም
ጉዳይ አንድ ቦታ ላይ መቆም
አለበት። ለውጥ አራማጅና
አደናቃፊ በውልና በግልጽ
ባልታወቀበት ሁኔታ የኢህአዴግ
ታሪካዊ ባህል የሆነው
የስም ታርጋ መለጠፍ ቢበቃ
በጎ ይመስለኛል ። አለበለዚያ
ለውጥ አደናቃፊዎች እነማን
እንደሆኑ በግልጽ ይነገረን
፣ እንወቃቸው። ሁሉም
ሰለ ለውጥ በሚናገርበት
በአሁኑ ወቅት ለውጥ አደናቃፊ
ማን እንደሆነ አይታወቅም
። ምን አይነት ለሚለው
ግን ሊያነጋግር ይችል
ይሆናል ።
የኢህአዴግ መንግሥት
የመንግስትነት ባህሪ የራቀው
ብቻ ሳይሆን ጥሩ ትያትረኛም
አልነበረም ። በህግና
በህገመንግስቱ የሚመራ
መንግሥትም አልነበረም
። የኢህአዴግ መንግሥት
በቀላል አገላለጽ የኮንትሮባንድ
/የማፊያዎች/ ሰብሰብ መንግሥት
እንጂ የህዝብ መንግሥትነት
ባህሪ አልነበሩትም ።
ሰውን ያህል ክቡር ፍጥነት
እንዴት ከሰው የማይጠበቅ
ድርጊት በሰው ዘር ጭካኔና
ሰብአዊ ግፍ ይፈፀምበታል?።
ለምንሰ ፍርድ ቤት የማያውቀው
እስርቤት ሰው ይታሰራል
?። የአንድ ወገን ችግርና
ሰቃይ ለአንዱ ካልተሰማው
እንዴት አብሮ መከተም
ይቻላል ?። እንዴትሰ ሰለ
አገር ማሰብ ይቻላል ?።
እንዴትስ ማህበራዊ ትስስር
ይመሰረታል ?። የመንግስት
አብይ የሰራ ሀላፊነት
የህዝብና የአገር ደህንነት
ማስከበር ሆኖ ሳለ ራሱ
መንግስት ህዝብ እሰቃይ
፣ አሳሪና ገራፊ ፣ ከሳሽና
መስካሪ ፣ ጠበቃና ዳኛ
መሆን እንዴት ይቻላል
?። መንግሥት ላጠፋው ጥፋት
ሀላፊነት መውሰድ የሚገባው
ራሱ መንግስት እንጂ ህዝብ
አይደለም ። በዜጎች ላይ
ሰቆቃና ግፍ የፈፀሙ የመንግስት
ሰራ ሀላፊዎች መቼም ቢሆን
ከፍትህ አይሰወሩም ።
የተደበቁት ብሔርም ሰብአዊ
መብት ጣሾች ከመጠየቅ
አያድናቸውም ። እውነታው
የህግ በላይነት ተቀብሎ
መኖር ነው ። በሰው ዘር
ላይ ግፍ ሰርቶ መደበቅ
እንዴት ይቻላል ?። ሰው
በፈለጉ ጊዜ የሚጣል ዕቃ
አይደለም ። ሰብዓዊ መብቱ
፣ በሰላም ሰርቶና አምርቶ
የኢኮኖሚ ፍላጎቱ ተጠብቆለት
የመኖር ዜግነታዊ መብት
እንዳለው አምኖና ያን
አክብሮ መምራትና ማስተዳደር
/ግቡዕ/ አሰፈላጊ ነበር
።
ህግ ለተላላፈ የመንግስት
ሹም ህዝብ ጥብቅና አይቆምም
። ሰብዓዊ መብት ለረገጠ
የመንግስት ሀላፊ የብሔር
ከለላ ለምን ያስፈልገዋል
?። ወንጀል የፈፀመ ሰው
ከለላ ማግኘት ያለበት
ከብሔር ሳይሆን ከህግ
ብቻ ነው ። ከዚህ ውጭ ሀቅ
የለም ።ችግሩ በኢትዮጵያ
ውስጥ ፍትሀዊ ፍትህ አለ
ወይ ነው ። የሁለንተናዊ
ለውጥ አቀንቃኝ ነኝ ብሎ
ከኢህአዴግ ሰረወ ሰርአት
ውስጥ በድንገት ይሁን
ታቅዶ የመንግስት በትረ
ሰልጣን የጨበጡ ዶክተር
አብይ አህመድ ባሉበት
የስልጣን ቦታ ውሰን የህግ
ጥሰቶች ፈፅመዋል። በመሆኑ
በህግ መጠየቅ ይኖርባቸዋል
። ከህግ ጥሰቶች አንዱ
ሜጀር ጀኔራል ክንፈ ዳኘው
በሜቴክ የአስተዳደር ጉዳይ
ለመጠየቅ በህግ ሰር በዋሉበት
ማግስት “ ምዕናባዊ “ የሚል
የተለመደ የመንግስት የፖለቲካ
ድራማ በጀኔራል ክንፈ
ዳኘው ላይ ፊልም ተሰርቶ
በመንግሥት መገናኛ ብዙሃን
ተሰራጨ ። ይህ በፍትህ
ሂደት ላይ የሚያስከትለው
ተፅዕኖ እጅግ የላቀ ነው
። ጀኔራሉ ከፍርድ ሂደት
በፊት በህዝብ ዘንድ ወንጀለኛ
አድርጎ መተወን የመንግስት
ሀላፊነት አልነበረም ።
በመሆኑ ጀኔራል ክንፈ
ዳኘው ላይ ኢፍትሐዊ ወንጀል
በመንግሥት ተፈፅሞባቸዋል
። በመሆኑ በጉዳዩ ላይ
ጠቅላይ ሚኒስቴር ዶክተር
አብይ አህመድ መከሰሰ
ይኖርባቸዋል ። ጀኔራሉ
ደግሞ በነፃ መለቀቅና
የሞራል ካሳ መከፈል ይገባቸዋል
። እውነታውም ይህ ብቻ
ነው ። ባለፈው ሳምንት
የተሰራው “ የፍትህ ሰቆቃ
“ የሚል የመንግስት የፖለቲካ
ፕሮፖጋንዳ ፊልም ውይም
መንግሰታዊ ትያትር የስብአዊ
መብት ወንጀሎች ይፈፀሙ
የነበሩ በትግርኛ ቋንቋ
ተናጋሪዎች ነው መባሉ
ትክክል አይደለም ብቻ
ሳይሆን አስነዋሪና የተዛባ
መረጃ ነው ። ትግርኛ ቋንቋ
ነው ።ማንም ሰው ወይም
ወንጀል ፈፃሚ ሊናገረው
ይችላል ። ሰለሆነም ወንጀል
ፈፃሚው የትግራይ ሰው
ነው ለማለት አያስደፍርም
።ለመረጃም አይጠቅምም
።በአጠቃላይ የድራማው
ተውኔት ትክክል አይደለም።
ጉዳዩ በትግራይ ህዝብ
ላይ ያነጣጠረ ሆነዋል
። የውስጥ የብሔር ግጭት
መንስኤና መነሻ ሊሆን
ይችላል ። ሆኖም ግን የተፈፀመው
ግፍ የሰው ዘር ይፈፅመዋል
ብየ ገምቼ አላውቅም ።
በጣም ያሳዝናል ። ሰይጣናዊ
ድርጊት የፈፀሙ የመንግስት
ሀላፊዎች በፍጥነት ለፍርድ
መቅረብ ይገባቸዋል ።
የኢትዮጵያ ህዝብ
የመንግስት ሰልጣን ተገን
በማድረግ ሌብነትና ሰብዓዊ
ወንጀል ሲፈፀሙና ሲያስፈፅሙ
ለነበሩ የመንግስት ሀላፊዎች
ከለላ ከመሆን ይልቅ አሳልፎ
ለህግ መሰጠት ይጠበቅበታል
። ይህ ካልሆነ የመንግስት
ሌቦች ብቻ ሳይሆኑ ማህበረሰቡ
ጋርም ችግር አለ ማለት
ነው ። ምክንያቱም ህዝብ
የመንግስት ሌቦችና ወንጀል
ፈፃሚዎች ፈፅሞ ሊተባበራቸው
አይችልም ። ላለማቅረብም
ምንም ምክንያት የለውም
። አንድ ጉዳይ በግል የማምንበት
ሀቅ ቢኖር ወንጀል ብሔር
የለውም ። ወንጀለኛ ከየትኛውም
ማህበረሰብ ምድብ ወይም
ዘር ሊሆን ይችላል ። ወንጀል
በብሔር ተዋፅኦ ክሰ አይመሰረትም።
የማንኛውም ማህበረሰብ
ወይም ብሔር ተወላጅ ወይም
ተወካይ በሃላፊነት በነበረበት
ወቅት የፈፀማቸው የህግ
ጥሰቶች ካሉ ከህግ ተጠያቂነት
ውጭ አይሆንም ። የአንድ
ብሔር ይሁን የሁለት ብሔር
በመንግሥት ሃላፊነት ሳሉ
ለፈፀሟቸው የህግ ጥሰቶች
ተጠያቂ ይሆናሉ ። የአንድ
ብሔር በተለያዩ የመንግስት
ሃላፊነት ከነበሩና የአገር
ሀብት ከዘረፉ እንዲሁም
ሰበአዊ መብት ከጣሱ በብሔራቸው
ሳይሆን በሰሩት የህግ
ጥሰት ይጠበቃል ። ወንጀል
በብሔር አይፈፀምም ።
ወንጀል በብሄር አይቀመርም
። ብሔር ላይ የሚያነጣጥር
የወንጀል ተጠያቂነት አለም
ላይ የለም ። ሲሆንም በሌለ
ጉዳይ ላይ በሰሜት መናወጥ
አሰፈላጊነቱ እምብዛም
አይታየኝም ። መሆን ያለበት
ወንጀል ፈፃሚዎች የትግራይ
ተወላጆች ወይም ትግርኛ
ተናጋሪዎች ብቻ አይደሉም
የሚለው ነው ። ሰለሆነም
ወንጀሎች ገና አልተነኩም
። ከአማራም ፣ ከኦሮሞም
፣ ከደቡብም ፣ ከጋምቤላም፣
በአጭሩ ከሁሉም ማህበረሰብ
ወንጀል የፈፀሙ አሉ ።
በመሆኑም እንደየ ወንጀል
ድርጊታቸው ለፍርድ መቅረብ
አለባቸው ።
በኢትዮጵያ የህግ
ልዕልና የሚያስፈፅሙ ተቋማት
ካልተተከሉ ሰላምና መረጋጋት
ለማስፈን መንግስት አቅም
አይኖረውም። በልዩ ልዩ
ኢኮኖሚያዊ / ማህበራዊ
/ እንዲሁም ፖለቲካዊ አሻጥሮች
የመዛልና የመፍረስ ሁኔታ
ሊያጋጥም ይችላል ። ውስጣዊ
መረጋጋት ካልሰፈነ የውጭ
ጣልቃ ገብነት ሊያንሰራፋ
ይችላል ። ፍትህ ማስፈን
ከሁሉም በላይ ነው ። በመሆኑም
በዚህ ዙሪያ የማይስማማ
ሰው ያለ አይመስለኝም
። የኢህአዴግ ሰርአትና
መንግሰታዊ አሰተዳደር
የተሸመደመደው የህግ በላይነት
ባለማክበሩ ነበር ። አሁንም
የኢህአዴግ ሰርአት በፍጥነት
ወንጀል ፈፃሚዎች ለፍርድ
ካላቀረበ በኢትዮጵያ ፖለቲካ
እንቅስቃሴ የመሳተፍ መብት
ሊነፈገው ይችላል ። የህግ
እገሌ ሊጣልበት ይችላል
። ሁኔታዎች ወደ እገዳው
የሚሄዱ ይመሰላሉ ። የብሔረ
አማራና ብሔረ ኦሮሞ የፖለቲካ
ሰያሜ ለውጥና የአደረጃጀት
ቅርፅ ለውጥ ማድረጋቸው
እንደ ምሳሌ ሊወሰድ ይችላል
። ኢህአዴግ በኢትዮጵያ
የፖለቲካ እንቅስቃሴ እንዳያደርግ
በህግ ከተከለከለ የኢህአዴግ
መሰረት ይናጋል። ፍፃሜውም
በኦሮማይ ይዘጋል ።
በኢትዮጵያ ህዝባዊ
አመኔታ ያላቸው የፍትህና
የዲሞክራሲ ተቋማት መመሰረት
የዜጎች ህልውና ጉዳይ
ብቻ ሳይሆን አገራዊ ግዴታም
ነው ። ከሰማንያ በላይ
የብሔር ፖርቲዎች ያላት
አገር ያለ ጠንካራ የፍትህና
የዲሞክራሲ ተቋማት /መትከል
/ አገራዊ ደህነት ሲታከልበት
አገር ይፈርሳል ፣ ህዝብ
ይበተናል ። የኢትዮጵያ
ብሔረሰቦች አንድ የጋራ
አገርና መንግሥት ያስፈልጋቸዋል
። የኢትዮጵያ ህዝቦች
በተናጠል ሳይሆን በጋራ
ለጋራ ጥቅሞቻቸው በአንድነት
መንፈስ መንቀሳቀስ ይኖርባቸዋል
። አንዱ ብሔር ኢትዮጵያ
ለኔ ምንድናት የሚል ጥያቄ
አንሰቶ መወያየትና መከራከር
አለበት ። የተናጠል ጉዞ
የሚያመጣው የማህበራዊ
/ኢኮኖሚ / ፖለቲካ / ጉዳት
እንጂ ጥቅም የለውም ።
በኢትዮጵያ ሁሉም ብሔረሰቦች
የማንነት እኩልነት አላቸው
። አሁን የሚያስፈልጋቸው
የነፃነት እኩልነት ነው
። እስከአሁን በነፃነት
የሚሞግት ማህበረሰብ በኢትዮጵያ
አላደገም ወይም አልተነቃቃም።
ለዚህ ችግር በምክንያትነት
ከሚቀርቡ ተግዳሮቶች ውስጥ
የማህበረሰቡ የትምህርት
ክህሎት እንዲሁም ሰር
ሰደድ ድህነት በዋናነት
ለአስረጅነት ይወሰዳሉ
።
በኢትዮጵያ የግዛት
ፖለቲካ እንጂ የማስተዳደር
ፖለቲካ ጭራሹን አልተለመደም
። የመንግስት ስልጣን
የወሰደ አካል የህዝብና
አገር መሪ መሆኑን መንፈቅ
ሳይሞላው ይረሳዋል ።
በአጭር ጊዜም ህዝባዊና
አገራዊ በደሎች ይፈፅማል
። ለተጠያቂነት ቦታ አይሰጥም
። ሰልጣንም በህዝብ ፍላጎት
አይለቅም ። ሰልጣን የሚለቀው
እንደ ውሻ በህዝባዊ ማዕበል
ተወግሮ ነው ። በኢትዮጵያ
አንድ የቆየና የተሳሳተ
የፖለቲካ ምልከታ አለ።
ይህም የእገሌ ብሔር ለዚህ
ያህል ዘመን ገዛ የሚል
የፖለቲካ እሳቤ የማህበረሰብ
የፖለቲካ ብስለት ችግር
መኖሩን በግልጽ ይጠቁማል
። ማን ገዛ እንጂ ማን ምን
ለህዝብና አገር መልካም
ሰራ ሠራ የሚል ማህበራዊ
አመለካከት እምብዛም የተለመደ
አይደለም ።ይህ አመለካከት
ባልተቀየረበት አገር ሁሉም
ህዝብ የጋራ የፖለቲካ
አመለካከት አይኖረውም
። የሚኖረው ብሔርተኛ
አመለካከት ነው ። በብሔሩ
ልክ የሚያስብ ማህበረሰብ
ደግሞ ቀጣይነት ብሔራዊ
ችግር ካልሆነ ብሔራዊ
እድገት በጭራሸ አያሰፍንም
። ከብሔር አመለካከት
ባሻገር ማሰብ በውል እጅጉኑ
ያሰፈልጋል ። ለጋራ እድገትና
ማህበራዊ ትስስር በብሔር
አሰተሳሰብና አመለካከት
የተቃኘ መሆን የለበትም
። የእኔ ብሔር የሚያስፈልገው
ያህል ሌላ ብሔርም እንደዚያ
ነው ። በተናጠል ፍትህ
፣ ዲሞክራሲ ፣ ነፃነት
፣ ሰላምና መረጋጋት ፣
እንዲሁም ኢኮኖሚያዊ እድገት
አይሳካም ። የእኔ ብሔር
ተጨቆነ ከማለት ችግሩ
የጋራ ነው ብሎ ማሰብ ለችግሩ
መፍትሔ ማግኘት ይቻላል
። በአንድ አገር የተናጠል
ችግር አይኖርም ። የአንድ
አገር ኢፍትሐዊ የፖለቲካ
ሰርአትና የፖለቲካ አሰተዳደር
ካለ አንድ ብሔር ለይቶ
አይጎዳም ። ለአንድ አገር
በጋራ መሰራትና ማሰብ
ያሰፈልጋል ።
በኢትዮጵያ በቀጣዩ
በመንግሥትም ሆነ በህዝብ
በጋራ መከናወን የሚገባቸው
አገራዊ ጉዳዮች የዜጎች
ሁለንተናዊ መብቶችና ደህንነቶች
የሚያስጠብቁ ተቋማት በፍጥነት
ማቋቋም ያሰፈልጋል ።
መንግሰት የሚመራው ህዝብ
ሳይሆን ህዝብ የሚመራው
መንግሥት መሰየም ይኖርበታል
። ዜግነታዊ መብት ጠያቂና
የዜግነት ግዴታ ፈፃሚ
የማህበረሰብ ሰርአት መተከል
ይኖርበታል ። ህዝቡ የመንግሥት
ዋልጌዎች ላይ ከፍተኛ
ክትትልና ቁጥጥር ብቻ
ሳይሆን ማዋረድና ማብጠልጠል
ጭምር /Naming and shaming / ሰራ መሰራት
ይኖርበታል ። የፍትህና
የዲሞክራሲ ተቋማት ፍፁም
ከፖለቲካ ጣልቃ ገብነት
የፀዱና በባለሞያዎች መተዳደር
ይኖሩባቸዋል ። የብሔር
ፖለቲካ ሳይሆን ለዘላቂ
ሰላም የዜግነት ፖለቲካ
እንዲሁም የብሔር መንግስት
ሳይሆን የህዝብ መንግስት
መመሰረት ጠቃሚነቱ የጎላ
ይሆናል ። ያልተማከለ
የአገር አሰተዳደር ሰርአት
/ ፌደራሊዝም/ ቋንቋን መሰረት
ያደረገ መሆን የለበትም
። ምክንያቱም ቋንቋ መነሻ
ያደረገ የፌዴራል አወቃቀር
ለማህበራዊ መፈናቀል ችግር
አንዱ ምክንያት ነው ።
ነፃ የህዝብ ሲቪክ ማህበረሰብ
መደራጀትና መጠናከር ይኖርባቸዋል
። ያለ ነፃ ሲቪክ ማህበረሰብ
ተሳትፎ ፍትሀዊ ፍትህና
ዲሞክራሲ እውን አይሆንም
። ሰራ አጥነት የበዛበት
አገር የተረጋጋ ሰላምና
የተመጣጠነ የማህበረሰብ
የኢኮኖሚ ለውጥ አይኖርም
። በመሆኑም መንግስት
ሰራ አጥነት ለመቀነስ
የተማረ ሆነ ያልተማረ
ያማከለ የኢኮኖሚ እቅዳቸው
መንደፍና መፅደቅ ይኖርባቸዋል
። የኢትዮጵያ ማህበረሰብ
/ ህዝብ / በብሔርና በጎጥ
ወርዶ ማሰብ እንደማይበጅ
መረዳት ይኖርበታል ።
በብሔር ደረጃ አስቦ ፣
የፖለቲካና ኢኮኖሚ ፖሊሲ
ሰርቶ የኢኮኖሚም ሆነ
ማህበራዊ ስኬት ያመጣል
አገር አለም ላይ የለም
። የአንድ አገር ህዝብ
አገራዊ ችግርም ሆነ ፀጋ
የህዝቦች የጋራ ችግርና
ፀጋ እንጂ የተወሰኑ ብሔረሰቦች
ችግር ወይም ፀጋ የሚሆንበት
ጊዜም የለም ።
በኢትዮጵያ እንደ
ህዝብ ያለብን ችግር የፖለቲካ
ስርአትና የነፃነት ችግር
አንጂ የብሔር ችግር የለም
።ማንም ብሔር ማንንም
ብሔር ላይ የፖለቲካም
ሆነ የኢኮኖሚ ጉዳት አያደርስም
፣ አይፈፀምም ።በኢትዮጵያ
የመናናቅ ማህበረሰብ
እንዲፈጠር ያደረገው የብሔር
ፖለቲካ ነው ። የብሔር
ፖለቲካ ብሔር ተኮር በመሆኑ
የሌላውን ብሔር ቁሰልና
ብሶት ለመሰማትና ለማየት
ያስቸግራል ። በአጠቃላይ
ከብሔርም ውጭ ያለ ማንኛውም
ብሔር ላይ ችግር ቢያጋጥመው
የደራሸነት መንፈስና ሰሜት
የቀዘቀዘና የዛለ ይሆናል
።አንድነት ለማሰፈንም
አዳጋች ይሆናል ። ከየትም
ማህበራዊ /ኢኮኖሚያዊ
/ እንዲሁም ፖለቲካዊ ጥቃት
ለመመልከት አሰቸጋሪ ይሆናል
። የውስጥ ህዝባዊ አመፅ
ለመቋቋምም አቅመ ቢሰ
ያደርጋል ። የብሔር ፖለቲካ
ያመጣው አንዱ ችግር የፍትህ
መዛባት ላይ አሰተያየትም
ሆነ የእርምት እርምጃ
ለመውሰድ ያስቸግራል ።
ለአብነት ያሀል = በእኔ
ብሔር ፖለቲካ መረጃዎች
የሚፈፀም ወንጀል እኔን
ወይም ብሔሩን እሰከ አልበደለ
ድረሰ ችግሩ እኔን አይመለከትም
። ይህ አመለካከት እጅግ
ይጎረብጣል ፣ ያማልም።
ችግሩ የእኔ ወገን ላይ
ባለመፈፀሙ ለእኔ ምን
ገዶኝ ከሆነ ጉዳዩ ታላቅ
ሰብዓዊ ስህተት ይሆናል
። ሌላው የብሔር ፖለቲካ
ችግር ከስሜታዊነት ያለፈ
ተግባር ለመስራት የሚቻል
አይሆንም ። የብሔር ፖለቲካ
በሀሳብ ሳይሆን ተያይዞ
በሰሜት ቁልቁል መድፋት
ነው ።
No comments:
Post a Comment